ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ሳሙኤል 20:34-38 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

34. ዮናታንም በታላቅ ቊጣ ከግብሩ ላይ ተነሣ፤ አባቱም ዳዊትን ስላዋረደው ወሩ በገባ በሁለተኛው ቀን ምግብ አልበላም።

35. በማግስቱ ጠዋት ዮናታን አንድ ትንሽ ልጅ አስከትሎ፣ ከዳዊት ጋር ወደ ተቃጠረበት ቦታ ሄደ፤

36. ልጁንም፣ “ሩጥ! የምሰዳቸውን ፍላጻዎች ፈልጋቸው” አለው፤ ልጁም በሮጠ ጊዜ፣ ከእርሱ አሳልፎ አንድ ፍላጻ ወረወረ።

37. ልጁም የዮናታን ፍላጻ ባረፈበት ስፍራ እንደ ደረሰ፤ ዮናታን ጠራውና፣ “ፍላጻው ካንተ ወዲያ ዐልፎ የለምን?” አለው።

38. እርሱም “ቶሎ በል! ፍጠን! አትቁም!” ሲል ጮኸበት፤ ልጁም ፍላጻዎቹን ሰብስቦ ወደ ጌታው ተመለሰ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ሳሙኤል 20