ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 1:44-54 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

44. ባላቅ ሲሞትም የባሶራ ሰው የሆነው የዛራ ልጅ ኢዮባብ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

45. ኢዮባብ ሲሞት የቴማን አገር ሰው የሆነው ሑሳም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

46. ሑሳም ሲሞት በሞዓብ ምድር ምድያምን ድል ያደረገው የባዳድ ልጅ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ። የከተማዪቱም ስም ዓዊት ተባለ።

47. ሃዳድም ሲሞት የመሥሬቃ ሰው የሆነው ሠምላ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

48. ሠምላም ሲሞት በወንዙ አጠገብ ያለችው የረሚቦት ሰው የሆነው ሳኡል በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

49. ሳኡልም ሲሞት የዓክቦር ልጅ የሆነው በኣልሐናንም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

50. በኣልሐናን ሲሞት ሀዳድ በእግሩ ተተክቶ ነገሠ። ከተማውም ፋዑ ትባል ነበር፤ ሚስቱ መሄጣብኤል ትባላለች፤ እርሷም የሜዛሃብ ልጅ የመጥሬድ ልጅ ነበረች።

51. ሀዳድም ሞተ። ዋና ዋናዎቹ የኤዶም ሕዝብ አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ቲምናዕ፣ ዓልዋ፣ የቴት፣

52. አህሊባማ፣ ኤላ፣ ፊኖን፣

53. ቄኔዝ፣ ቴማን፣ ሚብሳር፣

54. መግዲኤል፣ ዒራም። እነዚህ የኤዶም አለቆች ነበሩ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 1