ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 23:14-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. የእግዚአብሔር ሰው የሙሴ ወንዶች ልጆችም እንደ ሌዊ ነገድ ሆነው ተቈጠሩ።

15. የሙሴ ወንዶች ልጆች፤ጌርሳም፣ አልዓዛር።

16. የጌርሳም ዘሮች፤ሱባኤል።

17. የአልዓዛር ዘሮች፤የመጀመሪያው ረዓብያ ነበረ።አልዓዛር ሌሎች ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ የረዓብያ ወንዶች ልጆች ግን እጅግ ብዙ ነበሩ።

18. የይስዓር ወንዶች ልጆች፤የመጀመሪያው ሰሎሚት።

19. የኬብሮን ወንዶች ልጆች፤የመጀመሪያው ይሪያ፣ ሁለተኛው አማርያ፣ ሦስተኛው የሕዚኤል፣ አራተኛው ይቅምዓም ነበሩ።

20. የዑዝኤል ወንዶች ልጆች፤የመጀመሪያው ሚካ፣ ሁለተኛው ይሺያ ነበሩ።

21. የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤ሞሖሊ፣ ሙሲ።የሞሐሊ ወንዶች ልጆች፤አልዓዛርና ቂስ ነበሩ።

22. አልዓዛር ወንድ ልጅ ሳይወልድ ሞተ፤ ልጆቹ ሴቶች ብቻ ነበሩ፤ እነርሱንም የአጎታቸው የቂስ ልጆች አገቡአቸው።

23. የሙሲ ወንዶች ልጆች፤ሞሖሊ፣ ዔደር፣ ኢያሪሙት ባጠቃላይ ሦስት ናቸው።

24. እንግዲህ እነዚህ የቤተ ሰቡ አለቆች ሆነው እያንዳንዳቸው በየስማቸው ተመዝግበው የተቈጠሩት የሌዊ ዘሮች ናቸው፤ ዕድሜአቸውም ሃያና ከዚያ በላይ የሆናቸው በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ የሚያገለግሉ ነበሩ።

25. ዳዊት እንዲህ ብሎ ነበርና፣ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ዕረፍት ሰጥቷል፤ በኢየሩሳሌምም ለዘላለም ለመኖር መጥቷል፤

26. ሌዋውያን ከእንግዲህ ወዲህ ድንኳኑን ወይም የመገልገያ ዕቃውን ሁሉ መሸከም የለባቸውም።”

27. ዳዊት በሰጠው የመጨረሻ መመሪያ መሠረት የተቈጠሩት ሌዋውያን ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በላይ ነበረ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 23