ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 24:5-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ከአልዓዛርና ከኢታምር ዘሮች መካከል የመቅደሱ ሹማምትና የእግዚአብሔር ሹማምት ስለ ነበሩ፣ ያለ አድልዎ በዕጣ ለዩአቸው።

6. የሌዋዊው የናትናኤል ልጅ ጸሓፊው ሸማያ በንጉሡና በሹማምቱ፣ በካህኑ በሳዶቅ፣ በአብያታር ልጅ በአቤሜሌክ እንዲሁም በካህናቱና በሌዋውያኑ ቤተ ሰብ አለቆች ፊት ስማቸውን ጻፈ፤ የጻፈውም አንዱን ቤተ ሰብ ከአልዓዛር ሌላውን ደግሞ ከኢታምር በመውሰድ ነው፤

7. የመጀመሪያው ዕጣ ለዮአሪብ፣ሁለተኛውም ዕጣ ለዮዳሄ ወጣ፤

8. ሦስተኛው ለካሪም፣አራተኛው ለሥዖሪም፣

9. አምስተኛው ለመልክያ፣ስድስተኛው ለሚያሚን፣

10. ሰባተኛው ለአቆስ፣ስምንተኛው ለአብያ፣

11. ዘጠነኛው ለኢያሱ፣ዐሥረኛው ለሴኬንያ፣

12. ዐሥራ አንደኛው ለኤሊያሴብ፣ዐሥራ ሁለተኛው ለያቂም፣

13. ዐሥራ ሦስተኛው ለኦፖ፣ዐሥራ አራተኛው ለየሼብአብ፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 24