ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 9:32-40 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

32. በየሰንበቱ ለሚዘጋጀው ገጸ ኅብስትም ኀላፊነቱ የተሰጠው ከቀዓታውያን ወንድሞቻቸው መካከል ለአንዳንዶቹ ነበር።

33. የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች የነበሩት መዘምራኑ ደግሞ በቤተ መቅደሱ ክፍሎች ውስጥ እንዲኖሩና ከሌላው ሥራ ሁሉ ነጻ እንዲሆኑ ተደርጎ ነበር፤ ምክንያቱም ቀንና ሌሊት የሚሠሩት ሥራ ነበራቸው።

34. እነዚህ ሁሉ የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች ሲሆኑ፣ በትውልድ ሐረጋቸው መሠረት ተመዘገቡ፤ የሚኖሩትም በኢየሩሳሌም ነበረ።

35. የገባዖን አባት ይዒኤል የሚኖረው በገባዖን ነበረ፤የሚስቱም ስም መዓካ ይባላል።

36. የበኵር ልጁ ዓብዶን ሲሆን፣ የእርሱም ተከታዮች ዱር፣ ቂስ፣ በኣል፣ ኔር፣ ናዳብ፣

37. ጌዶር፣ አሒዮ፣ ዛኩር፣ ሚቅሎት ነበሩ።

38. ሚቅሎት ሳምአን ወለደ፤ እነርሱም ከዘመዶቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ይኖሩ ነበር።

39. ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስ ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦል ዮናታን፣ ሜልኪሳን፣ አሚናዳብን፣ አስበኣልን ወለደ።

40. የዮናታን ወንድ ልጅ፤መሪበኣል ነው፤ መሪበኣል ሚካን ወለደ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 9