አባትህና ሰዎቹ የማይበገሩ ተዋጊዎችና ግልገሎቿም እንደ ተነጠቁባት የዱር ድብ አስፈሪ መሆናቸውን አንተም ታውቃለህ፤ በተጨማሪም አባትህ በቂ ልምድ ያለው ነው፤ ሌሊቱን ከሰራዊቱ ጋር አያድርም፤