ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ሳሙኤል 22:11-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ፤በነፋስም ክንፍ መጠቀ።

12. ጨለማው በዙሪያው እንዲከበው፣ጥቅጥቅ ያለውም የሰማይ ዝናም ደመና እንዲሰውረው አደረገ።

13. በእርሱ ፊት ካለው ብርሃን፣የመብረቅ ብልጭታ ወጣ።

14. እግዚአብሔር ከሰማያት አንጐደጐደ፤የልዑልም ድምፅ አስተጋባ።

15. ፍላጻውን ሰድዶ ጠላቶቹን በተናቸው፤መብረቆቹንም ልኮ አወካቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ሳሙኤል 22