ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ሳሙኤል 22:20-35 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. ሰፊ ወደ ሆነ ስፍራ አወጣኝ፤በእኔ ደስ ስለ ተሰኘም አዳነኝ።

21. “እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ መለሰልኝ፤እንደ እጄም ንጹሕነት ብድራትን ከፈለኝ፤

22. የእግዚአብሔርን መንገድ ጠብቄአለሁና፤ከአምላኬም ዘወር ብዬ ክፉ ነገር አላደረግሁም።

23. ሕጉ ሁሉ በፊቴ ነው፤ከሥርዐቱም ዘወር አላልሁም።

24. በፊቱ ያለ ነውር ነበርሁ፤ራሴንም ከኀጢአት ጠብቄአለሁ።

25. እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ፣በፊቱም እንዳለኝ ንጽሕና ብድራትን ከፈለኝ።

26. “ለታማኝ ሰው አንተም ታማኝ መሆንህን፣ለቅን ሰው አንተም ቅን መሆንህን ታሳያለህ።

27. ለንጹሕ ሰው አንተም ንጹሕ መሆንህን፣ለጠማማ ሰው ግን አንተም ጠማማ መሆንህን ታሳያለህ።

28. አንተ የተጠቃውን ሕዝብ ታድናለህ፤ዐይንህ ግን ያዋርዳቸው ዘንድ፣ ትዕቢተኞችን ይመለከታል።

29. እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ መብራቴ ነህ፤ እግዚአብሔርም ጨለማዬን ያበራል።

30. በአንተ ርዳታ በጠላት ሰራዊት ላይ ወደፊት ገፍቼ እሄዳለሁ፤ በአምላኬም ኀይል ቅጥሩን እዘላለሁ።

31. “የአምላክ መንገዱ ፍጹም ነው፤ የእግዚአብሔርም ቃል የነጠረ ነው፤ለሚታመኑበትም ሁሉ ጋሻ ነው፤

32. ከእግዚአብሔር በቀር አምላክ ማን አለና፤ከአምላካችንስ በቀር ዐለት ማን ነው?

33. ኀይልን የሚያስታጥቀኝ፣መንገዴንም የሚያቀና እርሱ አምላኬ ነው።

34. እግሮቼን እንደ ብሆር እግር ያበረታል፤በከፍታዎችም ላይ አጽንቶ ያቆመኛል።

35. እጆቼን ለጦርነት ያሰለጥናል፤ክንዶቼም የናስ ቀስት ይገትራሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ሳሙኤል 22