ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ሳሙኤል 22:38-48 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

38. “ጠላቶቼን አሳደድሁ፤ አጠፋኋቸውም፤እስኪደመሰሱም ድረስ ወደ ኋላ አልተመለስሁም።

39. ፈጽሜ አጠፋኋቸው፤ ተመልሰውም መቆም አልቻሉም፤ከእግሬም ሥር ወድቀዋል።

40. ለጦርነት ኀይልን አስታጠቅኸኝ፣ተቃዋሚዎቼንም ከእግሬ ሥር አንበረከካቸው።

41. ጠላቶቼ ፊታቸውን አዙረው እንዲሸሹ አደረግሃቸው።ባላንጣዎቼንም ደመሰስኋቸው።

42. ለርዳታ ጮኹ፤ ያዳናቸው ግን አልነበረም፤ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እርሱ ግንአልመለሰላቸውም።

43. በምድር ላይ እንዳለ ትቢያ አድቅቄ ፈጨዃቸው፤በመንገድም ላይ እንዳለ ጭቃ ወቀጥኋቸው፤ ረገጥኋቸውም።

44. “በሕዝቤ ከተቃጣብኝ አደጋ አዳንኸኝ፤የመንግሥታትም ራስ አደረግኸኝ።የማላውቀው ሕዝብ ተገዛልኝ፤

45. ባዕዳን ሊለማመጡኝ መጡ፤እንደ ሰሙኝም ወዲያውኑ ይታዘዙኛል።

46. ባዕዳን ፈሩ፤ከምሽጋቸውም እየተንቀጠቀጡ ወጡ።

47. “እግዚአብሔር ሕያው ነው፤ ዐለቴ የተባረከ ይሁን፤የድነቴ ዐለት አምላኬ ከፍ ከፍ ይበል።

48. የሚበቀልልኝ አምላክ፣መንግሥታትንም ከሥሬ የሚያስገዛልኝ እርሱ ነው፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ሳሙኤል 22