ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ሳሙኤል 22:42-51 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

42. ለርዳታ ጮኹ፤ ያዳናቸው ግን አልነበረም፤ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እርሱ ግንአልመለሰላቸውም።

43. በምድር ላይ እንዳለ ትቢያ አድቅቄ ፈጨዃቸው፤በመንገድም ላይ እንዳለ ጭቃ ወቀጥኋቸው፤ ረገጥኋቸውም።

44. “በሕዝቤ ከተቃጣብኝ አደጋ አዳንኸኝ፤የመንግሥታትም ራስ አደረግኸኝ።የማላውቀው ሕዝብ ተገዛልኝ፤

45. ባዕዳን ሊለማመጡኝ መጡ፤እንደ ሰሙኝም ወዲያውኑ ይታዘዙኛል።

46. ባዕዳን ፈሩ፤ከምሽጋቸውም እየተንቀጠቀጡ ወጡ።

47. “እግዚአብሔር ሕያው ነው፤ ዐለቴ የተባረከ ይሁን፤የድነቴ ዐለት አምላኬ ከፍ ከፍ ይበል።

48. የሚበቀልልኝ አምላክ፣መንግሥታትንም ከሥሬ የሚያስገዛልኝ እርሱ ነው፤

49. እርሱ ከጠላቶቼ እጅ ነጻ ያወጣኛል።አንተ ከጠላቶቼ በላይ ከፍ ከፍ አደረግኸኝ፤ከጨካኝ ሰዎችም እጅ ታደግኸኝ።

50. ስለዚህ እግዚአብሔር ሆይ፤በመንግሥታት መካከል አመሰግንሃለሁ፤ ለስምህም ምስጋና እዘምራለሁ።

51. ለንጉሡ ታላቅ ድል ይሰጠዋል፤ለቀባው ለዳዊትና ለዘሩ፣ለዘላለም የማይለወጥ ፍቅሩን ያሳየዋል።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ሳሙኤል 22