ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ነገሥት 23:1-2 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ከዚያም ንጉሡ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሽማግሌዎች ሁሉ ጠራ።

2. የይሁዳን ሰዎች ሁሉ፣ የኢየሩሳሌምን ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ፣ ካህናቱንና ነቢያቱን ሁሉ ከልጅ እስከ ዐዋቂ አንድም ሰው ሳይቀር ይዞአቸው ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መጣ። በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የተገኘውንም የኪዳኑን መጽሐፍ ቃል በጆሮአቸው እንዲሰሙት በሙሉ አነበበላቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ነገሥት 23