ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ነገሥት 4:27-29 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

27. የእግዚአብሔር ሰው ወዳለበት ተራራ ስትደርስም እግሩ ላይ ተጠመጠመች፤ ግያዝ ሊያስለቅቃት ሲመጣ፣ የእግዚአብሔር ሰው ግን፣ “እጅግ አዝናለችና ተዋት! እግዚአብሔር ይህን ለምን ከእኔ እንደሰወረውና እንዳልነገረኝ አልገባኝም” አለ።

28. እርሷም፣ “ጌታዬ፤ ለመሆኑ እኔ ልጅ እንድትሰጠኝ ጠይቄህ ነበርን? ‘አጒል ተስፋ እንዳትሰጠኝ’ አላልሁህምን?” አለችው።

29. ኤልሳዕም ግያዝን፣ “እንግዲህ ወገብህን ታጠቅ፤ በትሬን ያዝና ሩጥ፤ መንገድ ላይ ሰው ብታገኝ ሰላም አትበል፤ ማንም ሰው ሰላም ቢልህ መልስ አትስጥ፤ በትሬንም በልጁ ፊት ላይ አድርግ” አለው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ነገሥት 4