ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ዜና መዋዕል 1:8-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. ሰሎሞን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “ለአባቴ ለዳዊት ታላቅ በጎነት አድርገህለታል፤ እኔንም በእግሩ ተክተህ አንግሠኸኛል።

9. አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ ያነገሥኸኝ ብዛቱ እንደ ትቢያ በሆነ ሕዝብ ላይ ስለ ሆነ፣ ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸው ተስፋ ይጽና።

10. ይህን ሕዝብ ለመምራት እንድችል፣ ጥበብና ዕውቀትን ስጠኝ፤ ይህ ካልሆነ ይህን ታላቅ ሕዝብህን ማን ሊገዛ ይችላል?”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ዜና መዋዕል 1