ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሆሴዕ 11:4-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. በሰው የርኅራኄ ገመድ፣በፍቅርም ሰንሰለት ሳብኋቸው፤ቀንበሩን ከጫንቃቸው ላይ አነሣሁላቸው፤ዝቅ ብዬም መገብኋቸው።

5. “ታዲያ ንስሓ መግባትን እምቢ በማለታቸው፣ወደ ግብፅ አይመለሱምን?አሦርስ አይገዛቸውምን?

6. በከተሞቻቸው ላይ ሰይፍ ይመዘዛል፤የበሮቻቸውን መወርወሪያ ይቈርጣል፤ስለ ክፉ ዕቅዳቸውም ይደመስሳቸዋል።

7. ሕዝቤ ከእኔ ዘወር ማለትን መረጡ፤ወደ ልዑል ቢጣሩም፣በምንም ዐይነት አያከብራቸውም።

8. “ኤፍሬም ሆይ፤ እንዴት እጥልሃለሁ?እስራኤል ሆይ፤ እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ?እንዴት እንደ አዳማ አደርግሃለሁ?እንዴትስ እንደ ሲባዮ እፈጽምብሃለሁ?ልቤ በውስጤ ተናወጠ፤ምሕረቴም ሁሉ ተነሣሥቶአል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሆሴዕ 11