ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሆሴዕ 7:10-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. የእስራኤል ትዕቢት በራሱ ላይ መሰከረበት፤ይህ ሁሉ ሆኖ ግን፣ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር አልተመለሰም፤እርሱንም አልፈለገም።

11. ኤፍሬም በቀላሉ እንደምትታለል፣አእምሮም እንደሌላት ርግብ ነው፤አንድ ጊዜ ወደ ግብፅ ይጣራል፤ሌላ ጊዜ ደግሞ ወደ አሦር ይዞራል።

12. ሲበሩ፣ መረቤን በላያቸው እዘረጋለሁ፤እንደ ሰማይ ወፎችም ጐትቼአወርዳቸዋለሁ፤ስለ ክፉ ሥራቸውም በጒባኤ መካከል እቀጣቸዋለሁ።

13. ወዮ ለእነርሱ፤ከእኔ ርቀው ሄደዋልና!ጥፋት ይምጣባቸው!በእኔ ላይ ዐምፀዋልና።ልታደጋቸው ፈለግሁ፤እነርሱ ግን በእኔ ላይ ሐሰት ይናገራሉ።

14. ከልባቸው ወደ እኔ አይጮኹም፤ነገር ግን በዐልጋቸው ላይ ሆነው ያለቅሳሉ።ስለ እህልና ስለ አዲስ የወይን ጠጅይሰበሰባሉ፤ነገር ግን ከእኔ ዘወር ብለዋል።

15. እኔ አሠለጠንኋቸው፤ አጠነከርኋቸውም፤እነርሱ ግን አደሙብኝ።

16. ወደ ከንቱ ነገር ተመለሱ፤ዒላማውን እንደሳተ ቀስት ናቸው፤መሪዎቻቸው ስለ ክፉ ቃላቸው፣በሰይፍ ይወድቃሉ፤በዚህም ምክንያት በግብፅ ምድር፣መዘባበቻ ይሆናሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሆሴዕ 7