ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሆሴዕ 9:11-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. የኤፍሬም ክብር እንደ ወፍ በሮ ይጠፋል፤መውለድ፣ ማርገዝና መፀነስ የለም።

12. ልጆችን ቢያሳድጉ እንኳ፣ልጅ አልባ እስኪሆኑ ድረስ እነጥቃቸዋለሁ፤ፊቴን ከእነርሱ በመለስሁ ጊዜ፣ወዮ ለእነርሱ

13. ኤፍሬምን እንደ ጢሮስ፣በመልካም ስፍራ ተተክሎ አየሁት፤አሁን ግን ኤፍሬም ልጆቹን፣ለነፍሰ ገዳዮች አሳልፎ ይሰጣል።”

14. እግዚአብሔር ሆይ፤ ስጣቸው፤ምን ትሰጣቸዋለህ?የሚጨነግፉ ማሕፀኖችን፣የደረቁ ጡቶችን ስጣቸው።

15. “በጌልገላ ካደረጉት ክፋታቸው ሁሉ የተነሣ፣እኔ በዚያ ጠላኋቸው፤ስለሠሩት ኀጢአት፣ከቤቴ አሳድዳቸዋለሁ፤ከእንግዲህም አልወዳቸውም፤መሪዎቻቸው ሁሉ ዐመፀኞች ናቸው።

16. ኤፍሬም ተመታ፤ሥራቸው ደረቀ፤ፍሬም አያፈሩም፤ልጆች ቢወልዱም እንኳ፣ተንከባክበው ያሳደጓቸውን ልጆቻቸውን እገድላለሁ።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሆሴዕ 9