ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሕዝቅኤል 32:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት፣ በዐሥራ ሁለተኛው ወር፣ በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤

2. “የሰው ልጅ ሆይ፤ ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን ሙሾ አውርድ፤ እንዲህም በለው፤“ ‘አንተ በሕዝቦች መካከል እንደ አንበሳ፣በባሕሮችም ውስጥ እንደ አስፈሪ አውሬ ነህ፤በወንዞችህ የምትንቦጫረቅ፣ውሃውን በእግርህ የምትመታ፣ምንጮችን የምታደፈርስ ነህ።

3. “ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ ‘ብዙ ሕዝብ ይዤ፣መረቤን በላይህ ላይ እጥላለሁ፤በመረቤም ጐትተው ያወጡሃል።

4. በምድር ላይ እጥልሃለሁ፤ሜዳም ላይ እዘረጋሃለሁ፤የሰማይ ወፎች ሁሉ እንዲሰፍሩብህ አደርጋለሁ፤የምድር አራዊት ሁሉ በመስገብገብ ይበሉሃል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሕዝቅኤል 32