ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 100:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፤

2. እግዚአብሔርን በደስታ አገልግሉት፤በፍስሓ ዝማሬ ፊቱ ቅረቡ።

3. እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን ዕወቁ፤እርሱ ፈጠረን፤ እኛም የእርሱ ነን፤እኛ ሕዝቡ የማሰማሪያው በጎች ነን።

4. በምስጋና ወደ ደጆቹ፣በውዳሴም ወደ አደባባዮቹ ግቡ፤አመስግኑት፤ ስሙንም ባርኩ፤

5. እግዚአብሔር ቸር፣ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና፤ታማኝነቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 100