ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 101:2-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. እንከን የማይገኝባትን መንገድ አጥብቄ እይዛለሁ፤አንተ ወደ እኔ የምትመጣው መቼ ነው?በቤቴ ውስጥ፣በንጹሕ ልብ እመላለሳለሁ።

3. በዐይኔ ፊት፣ክፉ ነገር አላኖርም።የከሓዲዎችን ሥራ እጠላለሁ፤ከእኔም ጋር አይጣበቅም።

4. ጠማማ ልብ ከእኔ ይርቃል፤ለክፋትም ዕውቅና አልሰጥም።

5. ባልንጀራውን በስውር የሚያማውን፣አጠፋዋለሁ፤ትዕቢተኛ ዐይንና ኵራተኛ ልብ ያለውን፣እርሱን አልታገሠውም።

6. ከእኔ ጋር ይኖሩ ዘንድ፣ዐይኖቼ በምድሪቱ ታማኞች ላይ ናቸው፤በንጽሕና መንገድ የሚሄድ፣እርሱ ያገለግለኛል።

7. አታላይ የሆነ ማንም ሰው፣በቤቴ ውስጥ አይኖርም፤ሐሰትን የሚናገር፣በፊቴ ቀና ብሎ አይቆምም።

8. በምድሪቱ ላይ ያሉትን ክፉዎች ሁሉ፣በየማለዳው አጠፋቸዋለሁ፤ክፉ አድራጊዎችንም ሁሉ፣ ከእግዚአብሔር ከተማ እደመስሳቸዋለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 101