ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 102:4-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ልቤ ዋግ እንደ መታው ሣር ደርቆአል፤እህል መብላትም ዘንግቻለሁ።

5. ከጩኸቴ ድምፅ የተነሣ፣ዐጥንቴ ከቈዳዬ ጋር ተጣበቀ።

6. የምድረ በዳ እርኩም መሰልሁ፤በፍርስራሽ መካከል እንዳለ ጒጒት ሆንሁ።

7. ያለ እንቅልፍ አድራለሁ፤በቤቴ ጒልላት ላይ እንዳለ ብቸኛ ወፍ ሆንሁ።

8. ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ ይዘልፉኛል፤የሚያክፋፉኝም ስሜን እንደ ርግማን ቈጥረውታል።

9. ዐመድ እንደ እህል ቅሜአለሁና፤መጠጤንም ከእንባ ጋር ቀላቅያለሁ።

10. ከቍጣህና ከመዓትህ የተነሣ፣ወደ ላይ አንሥተኸኝ የነበርሁትን መልሰህ ጣልኸኝ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 102