ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 102:6-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. የምድረ በዳ እርኩም መሰልሁ፤በፍርስራሽ መካከል እንዳለ ጒጒት ሆንሁ።

7. ያለ እንቅልፍ አድራለሁ፤በቤቴ ጒልላት ላይ እንዳለ ብቸኛ ወፍ ሆንሁ።

8. ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ ይዘልፉኛል፤የሚያክፋፉኝም ስሜን እንደ ርግማን ቈጥረውታል።

9. ዐመድ እንደ እህል ቅሜአለሁና፤መጠጤንም ከእንባ ጋር ቀላቅያለሁ።

10. ከቍጣህና ከመዓትህ የተነሣ፣ወደ ላይ አንሥተኸኝ የነበርሁትን መልሰህ ጣልኸኝ።

11. ዘመኖቼ እንደ ምሽት ጥላ ናቸው፤እኔም እንደ ሣር ደርቄአለሁ።

12. እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ለዘላለም በዙፋንህ ተቀምጠሃል፤ስምህም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።

13. ትነሣለህ፤ ጽዮንንም በርኅራኄ ዐይን ታያለህ፤ለእርሷ በጎነትህን የምታሳይበት ዘመን ነውና፤የተወሰነውም ጊዜ ደርሶአል።

14. አገልጋዮችህ በድንጋዮቿ ደስ ይሰኛሉ፤ለዐፈሯም ይሳሳሉ።

15. ሕዝቦች የእግዚአብሔርን ስም፣የምድርም ነገሥታት ሁሉ ክብርህን ይፈራሉ።

16. እግዚአብሔር ጽዮንን መልሶ ይሠራታልና፤በክብሩም ይገለጣል።

17. እርሱ ወደ ችግረኞች ጸሎት ይመለከታል፤ልመናቸውንም አይንቅም።

18. ወደ ፊት የሚፈጠር ሕዝብ እግዚአብሔርን ያወድስ ዘንድ፣ይህ ለመጪው ትውልድ እንዲህ ተብሎ ይጻፍ፤

19. “እግዚአብሔር በከፍታ ላይ ካለው መቅደሱ ወደ ታች ተመልክቶአልና፤ከሰማይም ሆኖ ምድርን አይቶአል፤

20. ይኸውም የእስረኞችን ጩኸት ይሰማ ዘንድ፣ሞት የተፈረደባቸውንም ያድን ዘንድ ነው።”

21. ስለዚህ የእግዚአብሔር ስም በጽዮን፣ምስጋናውም በኢየሩሳሌም ይታወጃል፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 102