ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 102:8-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ ይዘልፉኛል፤የሚያክፋፉኝም ስሜን እንደ ርግማን ቈጥረውታል።

9. ዐመድ እንደ እህል ቅሜአለሁና፤መጠጤንም ከእንባ ጋር ቀላቅያለሁ።

10. ከቍጣህና ከመዓትህ የተነሣ፣ወደ ላይ አንሥተኸኝ የነበርሁትን መልሰህ ጣልኸኝ።

11. ዘመኖቼ እንደ ምሽት ጥላ ናቸው፤እኔም እንደ ሣር ደርቄአለሁ።

12. እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ለዘላለም በዙፋንህ ተቀምጠሃል፤ስምህም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 102