ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 102:9-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. ዐመድ እንደ እህል ቅሜአለሁና፤መጠጤንም ከእንባ ጋር ቀላቅያለሁ።

10. ከቍጣህና ከመዓትህ የተነሣ፣ወደ ላይ አንሥተኸኝ የነበርሁትን መልሰህ ጣልኸኝ።

11. ዘመኖቼ እንደ ምሽት ጥላ ናቸው፤እኔም እንደ ሣር ደርቄአለሁ።

12. እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ለዘላለም በዙፋንህ ተቀምጠሃል፤ስምህም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።

13. ትነሣለህ፤ ጽዮንንም በርኅራኄ ዐይን ታያለህ፤ለእርሷ በጎነትህን የምታሳይበት ዘመን ነውና፤የተወሰነውም ጊዜ ደርሶአል።

14. አገልጋዮችህ በድንጋዮቿ ደስ ይሰኛሉ፤ለዐፈሯም ይሳሳሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 102