ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 103:11-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፣እንዲሁ ለሚፈሩት ምሕረቱ ታላቅ ናት።

12. ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ፣መተላለፋችንን በዚያው መጠን ከእኛ አስወገደ።

13. አባት ለልጆቹ እንደሚራራ፣ እግዚአብሔር ለሚፈሩት እንዲሁ ይራራል።

14. እርሱ አፈጣጠራችንን ያውቃልና፤ትቢያ መሆናችንንም ያስባል።

15. ሰው እኮ ዘመኑ እንደ ሣር ነው፤እንደ ዱር አበባ ያቈጠቍጣል፤

16. ነፋስ በነፈሰበት ጊዜ ግን ድራሹ ይጠፋል፤ምልክቱም በቦታው አይገኝም።

17. የእግዚአብሔር ምሕረት ግን፣ከዘላለም እስከ ዘላለም በሚፈሩት ላይ ነው፤ጽድቁም እስከ ልጅ ልጅ ድረስ በላያቸው ይሆናል፤

18. ኪዳኑን በሚጠብቁት ላይ፣ትእዛዙንም ለመፈጸም በሚተጉት ላይ ይሆናል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 103