ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 103:17-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. የእግዚአብሔር ምሕረት ግን፣ከዘላለም እስከ ዘላለም በሚፈሩት ላይ ነው፤ጽድቁም እስከ ልጅ ልጅ ድረስ በላያቸው ይሆናል፤

18. ኪዳኑን በሚጠብቁት ላይ፣ትእዛዙንም ለመፈጸም በሚተጉት ላይ ይሆናል።

19. እግዚአብሔር ዙፋኑን በሰማይ አጽንቶአል፤መንግሥቱም ሁሉን ትገዛለች።

20. እናንተ ለቃሉ የምትታዘዙ መላእክቱ፤ትእዛዙንም የምትፈጽሙ እናንተ ኀያላን፤ እግዚአብሔርን ባርኩ።

21. እናንተ ፈቃዱን የምትፈጽሙ አገልጋዮቹ፤ሰራዊቱ ሁሉ፣ እግዚአብሔርን ባርኩ።

22. እናንተ በግዛቱ ሁሉ የምትኖሩ፣ፍጥረቱ ሁሉ፣ እግዚአብሔርን ባርኩ፤ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 103