ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 104:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ፤ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ አንተ እጅግ ታላቅ ነህ፤ክብርንና ግርማን ለብሰሃል።

2. ብርሃንን እንደ ሸማ ተጐናጽፈሃል፤ሰማያትንም እንደ ድንኳን መጋረጃ ዘረጋህ፤

3. የእልፍኝህን አግዳሚ በውሆች ላይ አኖርህ፤ደመናትን ሠረገላህ አደረግህ፤በነፋስ ክንፍ ትሄዳለህ።

4. መላእክትህን መንፈስ፣አገልጋዮችህንም የእሳት ነበልባል ታደርጋለህ።

5. ለዘላለም እንዳትናወጥ፣ምድርን በመሠረቷ ላይ አጸናሃት።

6. በጥልቁ እንደ ልብስ ሸፈንሃት፤ውሆችም ከተራሮች በላይ ቆሙ።

7. በገሠጽሃቸው ጊዜ ግን ፈጥነው ሄዱ፤የነጐድጓድህንም ድምፅ በሰሙ ጊዜ ሸሹ።

8. በተራሮች ላይ ፈሰሱ፤ወዳዘጋጀህላቸው ስፍራ፣ወደ ሸለቆዎች ወረዱ።

9. ተመልሰው ምድርን እንዳይሸፍኑ፣አልፈውም እንዳይመጡ ድንበር አበጀህላቸው።

10. ምንጮችን በሸለቆ ውስጥ እንዲሄዱ አደረግህ፤በተራሮችም መካከል ይፈሳሉ፤

11. የዱር እንስሳትም ከዚያ ይጠጣሉ፤የሜዳ አህዮችም ጥማቸውን ይቈርጣሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 104