ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 104:18-30 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. ረጃጅሙ ተራራ የዋልያ መኖሪያ፣የዐለቱም ዋሻዎች የሽኮኮ መሸሸጊያ ናቸው።

19. ጨረቃን የወቅቶች መለያ አደረግሃት፤ፀሓይም የምትጠልቅበትን ጊዜ ታውቃለች።

20. ጨለማን ታመጣለህ፤ ሌሊትም ይሆናል፤የዱር አራዊትም ሁሉ በዚህ ጊዜ ወጥተው ይራወጣሉ።

21. የአንበሳ ግልገሎች ምግብ ፍለጋ ይጮኻሉ፤የሚበሉትንም ከእግዚአብሔር ይሻሉ።

22. ፀሓይ በወጣች ጊዜም ይመለሳሉ፤በየጐሬአቸውም ገብተው ይተኛሉ።

23. ሰውም ወደ ሥራው ይሄዳል፤እስኪመሽም በተግባሩ ላይ ይሰማራል።

24. እግዚአብሔር ሆይ፤ ሥራህ እንዴት ብዙ ነው!ሁሉን በጥበብ ሠራህ፤ምድርም በፍጥረትህ ተሞላች።

25. ይህች ባሕር ሰፊና የተንጣለለች ናት፤ታላላቅና ታናናሽ እንስሳት፣ስፍር ቍጥር የሌላቸውም ነፍሳት በውስጧ አሉ።

26. መርከቦች በላይዋ ይመላለሳሉ፤አንተ የፈጠርኸውም ሌዋታን በውስጧ ይፈነጫል።

27. ምግባቸውን በወቅቱ ትሰጣቸው ዘንድ፣እነዚህ ሁሉ አንተን ተስፋ ያደርጋሉ።

28. በሰጠሃቸውም ጊዜ፣አንድ ላይ ያከማቻሉ፤እጅህንም ስትዘረጋ፣በመልካም ነገር ይጠግባሉ።

29. ፊትህን ስትሰውር፣በድንጋጤ ይሞላሉ፤እስትንፋሳቸውንም ስትወስድባቸው ይሞታሉ፤ወደ ዐፈራቸውም ይመለሳሉ።

30. መንፈስህን ስትልክ፣እነርሱ ይፈጠራሉ፤የምድርንም ገጽ ታድሳለህ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 104