ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 104:27-35 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

27. ምግባቸውን በወቅቱ ትሰጣቸው ዘንድ፣እነዚህ ሁሉ አንተን ተስፋ ያደርጋሉ።

28. በሰጠሃቸውም ጊዜ፣አንድ ላይ ያከማቻሉ፤እጅህንም ስትዘረጋ፣በመልካም ነገር ይጠግባሉ።

29. ፊትህን ስትሰውር፣በድንጋጤ ይሞላሉ፤እስትንፋሳቸውንም ስትወስድባቸው ይሞታሉ፤ወደ ዐፈራቸውም ይመለሳሉ።

30. መንፈስህን ስትልክ፣እነርሱ ይፈጠራሉ፤የምድርንም ገጽ ታድሳለህ።

31. የእግዚአብሔር ክብር ለዘላለም ጸንቶ ይኑር፤ እግዚአብሔር በሥራው ደስ ይበለው፤

32. እርሱ ምድርን ሲመለከት፣ ትንቀጠቀጣለች፤ተራሮችም እርሱ ሲዳስሳቸው ይጤሳሉ።

33. በሕይወት ሳለሁ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ቆሜ እስከ ሄድሁ ድረስም አምላኬን እወድሳለሁ።

34. እኔ በእግዚአብሔር ደስ እንደሚለኝ፣የልቤ ሐሳብ እርሱን ደስ ያሰኘው።

35. ኀጥአን ከምድር ገጽ ይጥፉ፤ዐመፀኞች ከእንግዲህ አይገኙ።ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ፤ሃሌ ሉያ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 104