ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 105:38-45 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

38. እጅግ ፈርተዋቸው ነበርና፣ወጥተው ሲሄዱ ግብፅ ደስ አላት።

39. ደመናን እንደ መጋረጃ ዘረጋላቸው፤እሳትም በሌሊት አበራላቸው።

40. በለመኑትም ጊዜ፣ ድርጭት አመጣላቸው፤የሰማይንም እንጀራ አጠገባቸው።

41. ዐለቱን ሰነጠቀ፤ ውሃም ተንዶለደለ፤እንደ ወንዝም በበረሓ ፈሰሰ።

42. ለባሪያው ለአብርሃም የሰጠውን፣ቅዱስ የተስፋ ቃሉን አስቦአልና።

43. ሕዝቡን በደስታ፣ምርጦቹንም በእልልታ አወጣቸው።

44. የሌሎችን ሕዝቦች ምድር ሰጣቸው፤የእነዚህንም የድካም ፍሬ ወረሱ፤

45. ይህም ሥርዐቱን ይጠብቁ ዘንድ፣ሕጉንም ይፈጽሙ ዘንድ ነው።ሃሌ ሉያ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 105