ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 106:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሃሌ ሉያቸር ነውና፣ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ምሕረቱም ለዘላለም ነውና።

2. ስለ እግዚአብሔር ታላቅ ሥራ ማን ሊናገር ይችላል?ምስጋናውንስ ሁሉ ማን ተናግሮ ይጨርሳል?

3. ፍትሕ እንዳይዛነፍ የሚጠብቁ፣ጽድቅን ሁል ጊዜ የሚያደርጉ የተባረኩ ናቸው።

4. እግዚአብሔር ሆይ፤ ለሕዝብህ ሞገስ ስታድል አስበኝ፤በምታድናቸውም ጊዜ ርዳኝ፤

5. ይኸውም የምርጦችህን ብልጽግና አይ ዘንድ፣በሕዝብህ ደስታ ደስ ይለኝ ዘንድ፣ከርስትህም ክብር የተነሣ እጓደድ ዘንድ ነው።

6. እኛም እንደ አባቶቻችን ኀጢአት ሠራን፤በደልን፤ ክፉም አደረግን።

7. አባቶቻችን በግብፅ ሳሉ፣ታምራትህን አላስተዋሉም፤የምሕረትህን ብዛት አላሰቡም፤በባሕሩ አጠገብ፣ ገና ቀይ ባሕር አጠገብ ዐመፁብህ።

8. እርሱ ግን የኀይሉን ታላቅነት ለማሳወቅ፣ስለ ስሙ አዳናቸው።

9. ቀይ ባሕርን ገሠጸ፤ እርሱም ደረቀ፤በምድረ በዳ እንደሚታለፍ በጥልቅ ውሃ መካከል መራቸው።

10. ከባለጋራቸው እጅ አዳናቸው፤ከጠላትም እጅ ታደጋቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 106