ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 107:33-39 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

33. ወንዞችን ወደ ምድረ በዳ፣የውሃ ምንጮችንም ወደ ደረቅ ምድር ለወጠ።

34. ከነዋሪዎቿ ክፋት የተነሣ፣ፍሬያማዋን ምድር በጨው የተበከለች አደረጋት።

35. ምድረ በዳውን ወደ ውሃ መከማቻ፣ደረቁንም ምድር ወደ ውሃ ምንጭ ቀየረ።

36. የተራቡትን በዚያ አስቀመጠ፤የሚኖሩባትንም ከተማ ሠሩ።

37. በዕርሻውም ዘሩበት፤ ወይንም ተከሉ፤ብዙ ፍሬም አመረቱ።

38. ይባርካቸዋል፤ እነርሱም እጅግ ይበዛሉ፤የከብቶቻቸውም ብዛት እንዲያንስ አያደርግም።

39. በጭንቅ፣ በመከራና በሐዘን፣ቍጥራቸው አንሶ፣ ተዋርደው ነበር፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 107