ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 107:39-43 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

39. በጭንቅ፣ በመከራና በሐዘን፣ቍጥራቸው አንሶ፣ ተዋርደው ነበር፤

40. በመኳንንቱም ላይ መናቅን አዘነበባቸው፤መውጫ መግቢያው በማይታወቅ በረሓ ውስጥም አንከራተታቸው።

41. ችግረኞችን ግን ከጭንቀታቸው መዝዞ አወጣቸው፤ቤተ ሰባቸውንም እንደ በግ መንጋ አበዛ።

42. ልበ ቅኖች ይህን አይተው ሐሤት ያደርጋሉ፤ጥመትም ሁሉ አፏን ትዘጋለች።

43. እንግዲህ ማንም ብልህ ቢሆን፣ ይህን ነገር ልብ ይበል፤እርሱም የእግዚአብሔርን ምሕረት ያስተውላል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 107