ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 109:8-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. ዕድሜው ይጠር፤ሹመቱንም ሌላ ይውሰደው።

9. ልጆቹ ድኻ አደጎች ይሁኑ፤ሚስቱም መበለት ትሁን።

10. ልጆቹ ይንከራተቱ፤ ለማኞችም ይሁኑ፤ከፈረሰው ቤታቸውም ይሰደዱ።

11. ያለውን ሁሉ ዕዳ ጠያቂ ይውረሰው፤የድካሙንም ዋጋ ባዕዳን ይቀሙት።

12. ማንም ሰው ምሕረት አያድርግለት፤ለድኻ አደግ ልጆቹም የሚራራ አይኑር።

13. ዘሩ ተለይቶ ይጥፋ፤ስማቸውም በሚቀጥለው ትውልድ ይደምሰስ።

14. የአባቶቹ በደል በእግዚአብሔር ፊት ይታሰብ፤የእናቱም ኀጢአት አይደምሰስ።

15. መታሰቢያቸውን ከምድር ያጠፉ ዘንድ፣ኀጢአታቸው ሁል ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ይኑር፤

16. ችግረኛውንና ምስኪኑን፣ ልቡም የቈሰለውን፣እስከ ሞት አሳደደ እንጂ፣ምሕረት ያደርግ ዘንድ አላሰበምና።

17. መራገምን ወደደ፤ ወደ እርሱም መጣች፤በመባረክ ደስ አልተሰኘም፤በረከትም ከእርሱ ራቀች።

18. መርገምን እንደ ልብስ ለበሳት፤እርሷም እንደ ውሃ ወደ ውስጥ ሰውነቱ፤እንደ ዘይትም ወደ ዐጥንቱ ዘለቀች።

19. ገላውን እንደሚሸፍንበት ልብስ፣ዘወትር እንደሚታጠቀውም መቀነት ትሁነው።

20. እግዚአብሔር ለሚወነጅሉኝ ሰዎች፣በነፍሴም ላይ ክፉ ለሚናገሩ የሚከፍላቸው ይኸው ይሁን።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 109