ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 118:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ቸር ነውና አመስግኑት፤ምሕረቱም ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።

2. የእስራኤል ሕዝብ፣ “ምሕረቱ ለዘላለም ነው” ይበል።

3. የአሮን ቤት፣ “ምሕረቱ ለዘላለም ነው” ይበል።

4. እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሁሉ፣“ምሕረቱ ለዘላለም ነው” ይበሉ።

5. በተጨነቅሁ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ እግዚአብሔርም መለሰልኝ፤ ከመጠበብም አወጣኝ።

6. እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ነው፤ አልፈራም፤ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?

7. ይረዳኝ ዘንድ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ነው፤የጠላቶቼንም ውድቀት አያለሁ።

8. ሰውን መከታ ከማድረግ ይልቅ፣ በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 118