ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 118:15-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. በጻድቃን ድንኳን የእልልታና የሆታ ድምፅ፣እንዲህ እያለ ያስተጋባል፤“የእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ብርቱ ሥራ ሠራች፤

16. የእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ከፍ ከፍ አለች፤ የእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ብርቱ ሥራ ሠራች።

17. ተርፌ በሕይወት እኖራለሁ እንጂ አልሞትም፤ የእግዚአብሔርንም ሥራ ገና እናገራለሁ።

18. መገሠጹን እግዚአብሔር እጅግ ገሥጾኛል፤ነገር ግን ለሞት አሳልፎ አልሰጠኝም።

19. የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ፤በዚያ ገብቼ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።

20. ይህች የእግዚአብሔር ደጅ ናት፤ጻድቃን በእርሷ በኩል ይገባሉ።

21. ሰምተህ መልሰህልኛልና፣አዳኝም ሆነህልኛልና አመሰግንሃለሁ።

22. ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፣እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ።

23. እግዚአብሔር ይህን አደረገ፤ለዐይናችንም ድንቅ ናት።

24. እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤በእርሷ ሐሤት እናድርግ፤ ደስም ይበለን።

25. እግዚአብሔር ሆይ፤ እባክህ አድነን፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እባክህ አሳካልን።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 118