ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 118:20-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. ይህች የእግዚአብሔር ደጅ ናት፤ጻድቃን በእርሷ በኩል ይገባሉ።

21. ሰምተህ መልሰህልኛልና፣አዳኝም ሆነህልኛልና አመሰግንሃለሁ።

22. ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፣እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ።

23. እግዚአብሔር ይህን አደረገ፤ለዐይናችንም ድንቅ ናት።

24. እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤በእርሷ ሐሤት እናድርግ፤ ደስም ይበለን።

25. እግዚአብሔር ሆይ፤ እባክህ አድነን፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እባክህ አሳካልን።

26. በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው። ከእግዚአብሔር ቤት ባረክናችሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 118