ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 118:7-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. ይረዳኝ ዘንድ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ነው፤የጠላቶቼንም ውድቀት አያለሁ።

8. ሰውን መከታ ከማድረግ ይልቅ፣ በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል።

9. በገዦች ተስፋ ከማድረግ ይልቅ፣ በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል።

10. ሕዝቦች ሁሉ ከበቡኝ፤ነገር ግን በእግዚአብሔር ስም አስወግዳቸዋለሁ።

11. መክበቡንስ በየአቅጣጫው ከበቡኝ፤ነገር ግን በእግዚአብሔር ስም አስወግዳቸዋለሁ።

12. እንደ ንብ መንጋ ከበቡኝ፤ነገር ግን እንደሚነድ እሾኽ ከሰሙ፤በእርግጥም በእግዚአብሔር ስም አስወግዳቸዋለሁ።

13. ተገፍትሬ ልወድቅ ተንገደገድሁ፤ እግዚአብሔር ግን ረዳኝ።

14. እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤አዳኝ ሆነልኝ።

15. በጻድቃን ድንኳን የእልልታና የሆታ ድምፅ፣እንዲህ እያለ ያስተጋባል፤“የእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ብርቱ ሥራ ሠራች፤

16. የእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ከፍ ከፍ አለች፤ የእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ብርቱ ሥራ ሠራች።

17. ተርፌ በሕይወት እኖራለሁ እንጂ አልሞትም፤ የእግዚአብሔርንም ሥራ ገና እናገራለሁ።

18. መገሠጹን እግዚአብሔር እጅግ ገሥጾኛል፤ነገር ግን ለሞት አሳልፎ አልሰጠኝም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 118