ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 124:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እስራኤል እንዲህ ይበል፦“እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን ኖሮ፣

2. ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን ኖሮ፣

3. ቍጣቸው በላያችን በነደደ ጊዜ፣በቁመናችን በዋጡን ነበር፤

4. ጐርፍ ባጥለቀለቀን፣ፈረሰኛው ውሃ ባሰጠመን፣

5. ደራሽ ውሃም ጠራርጎ በወሰደን ነበር።

6. በጥርሳቸው ከመዘንጠል የጠበቀን፣ እግዚአብሔር ይባረክ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 124