ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 126:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፣ሕልም እንጂ እውን አልመሰለንም።

2. በዚያን ጊዜ አፋችን በሣቅ፣እንደበታችንም በእልልታ ተሞላ፤በዚያን ጊዜም በሕዝቦች መካከል፣“እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገላቸው” ተባለ።

3. እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገልን፤እኛም ደስ አለን።

4. እግዚአብሔር ሆይ፤ በነጌቭ እንዳሉ ጅረቶች፣ምርኳችንን መልስ።

5. በእንባ የሚዘሩ፣በእልልታ ያጭዳሉ።

6. ዘር ቋጥረው፣እያለቀሱ የተሰማሩ፣ነዶአቸውን ተሸክመው፣እልል እያሉ ይመለሳሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 126