ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 130:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ ከጥልቅ ወደ አንተ እጮኻለሁ።

2. ጌታ ሆይ፤ ድምፄን ስማ፤ጆሮዎችህ የልመናዬን ቃል፣የሚያዳምጡ ይሁኑ።

3. እግዚአብሔር ሆይ፤ ኀጢአትን ብትቈጣጠር፣ጌታ ሆይ፤ ማን ሊቆም ይችላል?

4. ነገር ግን በአንተ ዘንድ ይቅርታ አለ፤ስለዚህም ልትፈራ ይገባሃል።

5. እግዚአብሔርን ደጅ እጠናለሁ፤ ነፍሴም በትዕግሥት ትጠብቀዋለች፤በቃሉም ተስፋ አደርጋለሁ።

6. ዘብ ዐዳሪ ንጋትን ከሚጠባበቅ ይልቅ፣አዎን፤ ዘብ ዐዳሪ ንጋትን ከሚጠባበቅ ይልቅ፣ነፍሴ ጌታን ትጠባበቃለች።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 130