ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 132:5-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ለእግዚአብሔር ስፍራን፣ለያዕቆብም ኀያል አምላክ ማደሪያን እስካገኝ ድረስ።”

6. እነሆ፤ በኤፍራታ ሰማነው፤በቂርያትይዓሪም አገኘነው።

7. “ወደ ማደሪያው እንግባ፤እግሮቹ በሚቆሙበት ቦታ እንስገድ።

8. እግዚአብሔር ሆይ፤ ተነሥ፤አንተና የኀይልህ ታቦት ወደ ማረፊያህ ስፍራ ሂዱ።

9. ካህናትህ ጽድቅን ይልበሱ፤ቅዱሳንህም እልል ይበሉ።”

10. ስለ አገልጋይህ ስለ ዳዊት ስትል፣የቀባኸውን ሰው አትተወው።

11. እግዚአብሔር ለዳዊት በእውነት ማለ፤በማይታጠፍም ቃሉ እንዲህ አለ፤“ከገዛ ራስህ ፍሬ፣በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ።

12. ወንዶች ልጆችህ ኪዳኔን፣የማስተምራቸውንም ምስክርነቴን ቢጠብቁ፣ልጆቻቸው በዙፋንህ ላይ፣ለዘላለም ይቀመጣሉ።

13. እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፣ማደሪያውም ትሆን ዘንድ ወዶአልና እንዲህ አለ፤

14. “ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት፤ፈልጌአታለሁና በእርሷ እኖራለሁ።

15. እጅግ አትረፍርፌ እባርካታለሁ፤ድኾቿን እንጀራ አጠግባለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 132