ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 137:1-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በባቢሎን ወንዞች አጠገብ፣ በዚያ ተቀምጠን ሳለን፣ጽዮን ትዝ ባለችን ጊዜ አለቀስን።

2. እዚያም በአኻያ ዛፎች ላይ፣በገናዎቻችንን ሰቀልን።

3. የማረኩን በዚያ እንድንዘምርላቸው ጠየቁን፤የሚያሠቃዩን የደስታ ዜማ ፈለጉብን፤ደግሞም፣ “ከጽዮን መዝሙሮች አንዱን ዘምሩልን” አሉን።

4. የእግዚአብሔርን ዝማሬ፣እንዴት በባዕድ ምድር እንዘምር!

5. ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ብረሳሽ፣ቀኝ እጄ ትክዳኝ።

6. ሳላስታውስሽ ብቀር፣ኢየሩሳሌምን የደስታዬ ቍንጮ ባላደርግ፣ምላሴ ከትናጋዬ ጋር ትጣበቅ።

7. እግዚአብሔር ሆይ፤ ኢየሩሳሌም በወደቀችበት ቀን፣ኤዶማውያን እንዴት እንደ ዛቱ ዐስብ፤ደግሞም፣ “አፍርሷት፤ፈጽማችሁ አፈራርሷት!” አሉ።

8. አንቺ አጥፊ የሆንሽ የባቢሎን ልጅ ሆይ፤በእኛ ላይ ስለ ፈጸምሺው ድርጊት፣የእጅሽን የሚሰጥሽ የተመሰገነ ነው፤

9. ሕፃናትሽንም ይዞ፣በዐለት ላይ የሚፈጠፍጥ የተመሰገነ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 137