ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 137:4-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. የእግዚአብሔርን ዝማሬ፣እንዴት በባዕድ ምድር እንዘምር!

5. ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ብረሳሽ፣ቀኝ እጄ ትክዳኝ።

6. ሳላስታውስሽ ብቀር፣ኢየሩሳሌምን የደስታዬ ቍንጮ ባላደርግ፣ምላሴ ከትናጋዬ ጋር ትጣበቅ።

7. እግዚአብሔር ሆይ፤ ኢየሩሳሌም በወደቀችበት ቀን፣ኤዶማውያን እንዴት እንደ ዛቱ ዐስብ፤ደግሞም፣ “አፍርሷት፤ፈጽማችሁ አፈራርሷት!” አሉ።

8. አንቺ አጥፊ የሆንሽ የባቢሎን ልጅ ሆይ፤በእኛ ላይ ስለ ፈጸምሺው ድርጊት፣የእጅሽን የሚሰጥሽ የተመሰገነ ነው፤

9. ሕፃናትሽንም ይዞ፣በዐለት ላይ የሚፈጠፍጥ የተመሰገነ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 137