ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 143:9-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተን መሰወሪያ አድርጌአለሁና፣ከጠላቶቼ አድነኝ።

10. አንተ አምላኬ ነህና፣ፈቃድህን እንድፈጽም አስተምረኝ፤መልካሙ መንፈስህም፣በቀናችው መንገድ ይምራኝ።

11. እግዚአብሔር ሆይ፤ ስለ ስምህ ሕያው አድርገኝ፤በጽድቅህም ነፍሴን ከመከራ አውጣት።

12. ጠላቶቼንም ለእኔ ስላለህ ምሕረት ደምስሳቸው፤እኔ ባሪያህ ነኝና፣ነፍሴን የሚያስጨንቋትን ሁሉ አጥፋቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 143