ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 144:2-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. እርሱ አፍቃሪ አምላኬና ጽኑ ዐምባዬ ነው፤ምሽጌና ታዳጊዬ፣የምከለልበትም ጋሻዬ ነው፤ሕዝቤን የሚያስገዛልኝም እርሱ ነው።

3. እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህን ያህል በልብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድን ነው?ታስበውስ ዘንድ የሰው ልጅ እስከዚህ ምንድን ነው?

4. ሰው እንደ እስትንፋስ ነው፤ዘመኑም ፈጥኖ እንደሚያልፍ ጥላ ነው።

5. እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰማያትህን ሰንጥቀህ ውረድ፤ይጤሱም ዘንድ ተራሮችን ዳስስ።

6. የመብረቅ ብልጭታ ልከህ በትናቸው፤ፍላጻህን ሰደህ ግራ አጋባቸው።

7. እጅህን ከላይ ዘርጋ፤ከኀይለኛ ውሃ፣ከባዕዳንም እጅ፣ታደገኝ፤ አድነኝም፤

8. አንደበታቸው ሐሰትን ይናገራል፤ቀኝ እጃቸውም የቅጥፈት ቀኝ እጅ ናት።

9. አምላክ ሆይ፤ አዲስ ቅኔ እቀኝልሃለሁ፤ዐሥር አውታር ባለው በገና እዘምርልሃለሁ።

10. ነገሥታትን ድል የሚያጐናጽፍ፣ባሪያውን ዳዊትን ከሚጐዳ ሰይፍ የሚያድነው እርሱ ነው።

11. አንደበታቸው ሐሰትን ከሚናገር፣ቀኝ እጃቸው የቅጥፈት ቀኝ እጅ ከሆነችው፣ከባዕዳን እጅ፣ታደገኝ፤ አድነኝም።

12. ወንዶች ልጆቻችን በወጣትነታቸው፣የተሟላ ዕድገት እንዳገኘ ተክል፣ሴቶች ልጆቻችንም ቤተ መንግሥት ለማስጌጥ፣እንደ ተቀረጹ የማእዘን ዐምዶች ይሁኑ።

13. ጐተራዎቻችን በተለያየ የእህል ዐይነት፣የተሞሉ ይሁኑ፤በጎቻችን እስከ ሺህ ይውለዱ፤በመስኮቻችንም እስከ ዐሥር ሺህ ይባዙ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 144