ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 144:6-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. የመብረቅ ብልጭታ ልከህ በትናቸው፤ፍላጻህን ሰደህ ግራ አጋባቸው።

7. እጅህን ከላይ ዘርጋ፤ከኀይለኛ ውሃ፣ከባዕዳንም እጅ፣ታደገኝ፤ አድነኝም፤

8. አንደበታቸው ሐሰትን ይናገራል፤ቀኝ እጃቸውም የቅጥፈት ቀኝ እጅ ናት።

9. አምላክ ሆይ፤ አዲስ ቅኔ እቀኝልሃለሁ፤ዐሥር አውታር ባለው በገና እዘምርልሃለሁ።

10. ነገሥታትን ድል የሚያጐናጽፍ፣ባሪያውን ዳዊትን ከሚጐዳ ሰይፍ የሚያድነው እርሱ ነው።

11. አንደበታቸው ሐሰትን ከሚናገር፣ቀኝ እጃቸው የቅጥፈት ቀኝ እጅ ከሆነችው፣ከባዕዳን እጅ፣ታደገኝ፤ አድነኝም።

12. ወንዶች ልጆቻችን በወጣትነታቸው፣የተሟላ ዕድገት እንዳገኘ ተክል፣ሴቶች ልጆቻችንም ቤተ መንግሥት ለማስጌጥ፣እንደ ተቀረጹ የማእዘን ዐምዶች ይሁኑ።

13. ጐተራዎቻችን በተለያየ የእህል ዐይነት፣የተሞሉ ይሁኑ፤በጎቻችን እስከ ሺህ ይውለዱ፤በመስኮቻችንም እስከ ዐሥር ሺህ ይባዙ።

14. ከብቶቻችን ይክበዱ፤አይጨንግፉ፤ አይጥፉም።እኛም በምርኮ አንወሰድ፤በአደባባዮቻችንም ዋይታ አይሰማ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 144