ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 145:11-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ስለ መንግሥትህ ክብር ይናገራሉ፤ስለ ኀይልህም ይነጋገራሉ፤

12. በዚህም ብርቱ ሥራህን፣የመንግሥትህንም ግርማ ክብር ያስታውቃሉ።

13. መንግሥትህ የዘላለም መንግሥት ናት፤ግዛትህም ለትውልድ ሁሉ ጸንቶ ይኖራል። እግዚአብሔር ቃሉን ሁሉ ይጠብቃል፤በሥራውም ሁሉ ቸር ነው።

14. እግዚአብሔር የሚንገዳገዱትን ሁሉ ይደግፋል፤የወደቁትንም ሁሉ ያነሣል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 145