ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 145:7-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. የበጎነትህን ብዛት በደስታ ያወሳሉ፤ስለ ጽድቅህም በእልልታ ይዘምራሉ።

8. እግዚአብሔር ቸር ነው፤ ርኅሩኅም ነው፤ለቍጣ የዘገየ፣ ምሕረቱ የበዛ።

9. እግዚአብሔር ለሁሉ ቸር ነው፤ምሕረቱም በፍጥረቱ ሁሉ ላይ ነው።

10. እግዚአብሔር ሆይ፤ ፍጥረትህ ሁሉ ያመሰግንሃል፤ቅዱሳንህም ይባርኩሃል።

11. ስለ መንግሥትህ ክብር ይናገራሉ፤ስለ ኀይልህም ይነጋገራሉ፤

12. በዚህም ብርቱ ሥራህን፣የመንግሥትህንም ግርማ ክብር ያስታውቃሉ።

13. መንግሥትህ የዘላለም መንግሥት ናት፤ግዛትህም ለትውልድ ሁሉ ጸንቶ ይኖራል። እግዚአብሔር ቃሉን ሁሉ ይጠብቃል፤በሥራውም ሁሉ ቸር ነው።

14. እግዚአብሔር የሚንገዳገዱትን ሁሉ ይደግፋል፤የወደቁትንም ሁሉ ያነሣል።

15. የሁሉ ዐይን አንተን በተስፋ ይጠብቃል፤አንተም ምግባቸውን በወቅቱ ትሰጣቸዋለህ።

16. አንተ እጅህን ትዘረጋለህ፤የሕያዋን ፍጥረታትንም ሁሉ ፍላጎት ታረካለህ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 145