ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 150:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን በመቅደሱ አመስግኑት፤በታላቅ ጠፈሩ አወድሱት።

2. ስለ ብርቱ ሥራው አመስግኑት፤እጅግ ታላቅ ነውና ወድሱት።

3. በመለከት ድምፅ አመስግኑት፤በበገናና በመሰንቆ ወድሱት።

4. በከበሮና በሽብሸባ አመስግኑት፤በባለ አውታር መሣሪያና በእምቢልታ አወድሱት።

5. ተርገብጋቢ ድምፅ ባለው ጸናጽል አመስግኑት፤ድምፀ መልካም በሆነ ጸናጽል ወድሱት።

6. እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚእብሔርን ያመስግን።ሃሌ ሉያ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 150