ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 18:4-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. የሞት ገመድ አነቀኝ፤የጥፋት ጐርፍም አጥለቀለቀኝ።

5. የሲኦል ገመድ ተጠመጠመብኝ፤የሞት ወጥመድም ተጋረጠብኝ።

6. በተጨነቅሁ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤እንዲረዳኝም ወደ አምላኬ ጮኽሁ፤እርሱም ከመቅደሱ ድምፄን ሰማ፤ጩኸቴም ከፊቱ ደረሰ፤ ወደ ጆሮውም ገባ።

7. ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ተናወጠችም፤የተራሮችም መሠረት ተናጋ፤ጌታ ተቈጥቶአልና ተንቀጠቀጡ።

8. ከአፍንጫው ጢስ ወጣ፤የሚባላ እሳት ከአፉ፤የፍም ነበልባል ከእርሱ ፈለቀ።

9. ሰማያትን ሰንጥቆ ወረደ፤ከእግሩም በታች ጥቍር ደመና ነበረ።

10. በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ፤በነፋስም ክንፍ መጠቀ።

11. ጨለማን መሰወሪያው፣ በዙሪያውም አጐበሩ አደረገው፤በዝናብ አዘል ጥቍር ደመናም ተሸፈነ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 18